Published On: Sun, Nov 6th, 2016

Conclusion- Let Us Walk You Through The Ethiopian History Before And Now With The current Politics !

 ከ1930 -2012 ድረስ ኢትዮጵያን የመሩዋት መሪዎች ሉዐላዊነቱዋን እንዴት አስጠብቀው አለፉ !
ይህ ገጽ የሶስቱን መሪዎች በሃገር ሉአላዊነት ላይ ብቻ ምን አይነት ስራ ሰርተው እንዳለፉ በአጭሩ የሚያሳይ ነው

the-three-leaders

                                  ንጉስ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
                ከ1930-1974 ኢትዮጵያ ይሕን ትመስል ነበር !

Ethiopia-carta

አንድ ሀገር አንድ ሕዝብ በቁዋንቃ እና በእምነት የግጭት ታሪክ የሌለው ተቻችሎ ፣ ተስማምቶና ተዋዶ በሰላም Haile_selassie-3እንዲኖር ያደረጉ ከመሆናቸውም በላይ እንኩዋንስ የኢትዮጵያን የአፍሪካን አንድነት እንዲመሰረት ያደረጉና የሐገራቸውን አንድነቱዋን አስጠብቀው ያለፉ መሪ ነበሩ  !
በብዙ አፍሪካውያን ዘንድም የአንድነት አባት በመባል ከሚጠሩ ቀደምት መሪዎች አንዱ እንደሆኑ ይነገራል !

                                ፕረዘዳንት መንግስቱ ሃይለማሪያም
                      ወታደራዊው ኮሚኒስት መንግስት : ከ1974 -1991  

Ethiopia-carta-2

mengistu-with-mandela

አንድ ሀገር አንድ ሕዝብ በቁዋንቃ እና በዘር የግጭት ታሪክ የሌለው ተቻችሎ ተስማምቶና ተዋዶ በሰላም እንዲኖር ያደረጉ ከመሆናቸውም በላይ በቀኝ ግዛት ውስጥ ለነበሩ ሀገሮች የነጻነት ትግል የረዱ መሪ ነበሩ !
ነገር ግን ከጅምሩ ከወራሪዋ ሱማሊያ ቀጥሎም ከኤርትራ እና ከትግራይ ተገንጣይ ሐይሎች ጋር በመዋጋት የሐገራቸውን ሉአላዊነት ለማስከበር የአገዛዝ ዘመናቸውን  ሙሉ በውጊያ ያሳለፉ ናቸው : ይሁን እንጂ  ህዝቦች በነጻነት የሚፈልጉትን ማምለክ የማይችሉበት የኮምኒስት ስርአት እና በአንድ የኮሚኒስት ፓርቲ ብቻ የምትመራ ሀገር አድርገዋት ነበረ : ሆኖም ግን ይህ የሐይማኖት ነጻነት መነፈግ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አላናጋም ህዝቦችዋንም አላለያየም ፣ አልከፉፈለም ፣ አንድነታቸውም እንዲናጋ የሚያደርግ ቁስል ጥሎ አላለፈም !

ታላቁ ባለ ራእይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ  ከ1991-2012 የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር መሪ ነበሩ TPLF (EPRDF)

     meles    tplfsymbol                                                ethiopia-carta3

በ1993 ኢትዮጵያ ይህን መሰለች !
በመቀጠልም በ2007 (1999 Ec)ያለ ሕዝቡ እውቅና እና ፈቃድ በገዛ ውሳኔአቸው ይህን የሀገራችንን ክፍል በታሪክ የድንበር ችግርም ሆነ ግጭት ለሌለን ለሱዳን ለመስጠት የተስማሙ እንደሆነ በተለያዩ የኢንተርኔት ድህረ ገጾች በየጊዜው መዘገቡ አዲስ አይደልም : መቸም እሳት በሌለበት ጭስ አይጨስም እንደሚባለው ሁሉ ይህ ለሱዳን ሊሰጥ ነው የተባለው የመሬት መጠን የሚያዋስነው ድንበር በርዝመት ሲለካ 725 km ሲሆን ተቅላላ ስፋት ደግሞ 250 km² ወይም 600, 000 ኤከር (250,000,000 m²) ለም መሬት እንደሆነ በሰፊው እየተነገረ ነው:ከሁሉም በላይ የሚገርመውና የሚያሳዝነው  በዚህ መሬት ላይ ሰፍረው ይኖሩ የነበሩ የ17 መንደር ነዋሪዎች ኢትዮጵይዊያን ወገኖቻችን እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል ማወቅ ባይቻልም ሰብአዊ ህሊና ላለው ሰው ግን ማሰቡም ሆነ መገመቱ በጣም ይከብዳል:

the-north-west-land-for-sudanእኚሁ ድንቅና ታላቁ ባለ ራእይ በመባል በወዳጆቻቸው እና በትግል አጋሮቻቸው የሚሞካሹት መለስ ዜናዊ የሰው ልጅ ክፉ ጠላት የሆነው ሞት ባይቀድማቸው ኖሮ ከኬንያም ጋር ያለንንና ሰምተን የማናውቀውን የድንበር ችግር ሞያሌን በመስጠት ይገላግሉን ነበር በማለት እየተሳለቁ ሐሳባቸውን የቸሩ ብዙዎች እንደሆኑ ይነገራል በማያያዝም እንዲህ አይነቱ ታላቅ መሪ በአጭሩ መቀጨታችው የብዙዎችን አንጀት አቃጥሎ ያለፈ ቢሆንም በቦታቸው የተተኩት የትግል አጋሮቻቸው ግን የመለስን ራእይ ለመፈጸም ወደ ሁዋላ እንደማይሉ ቃል በገቡት መሰረት ከፍጻሜ ለማድረስ ላይ ታች እያሉ እንደሆነ በሰፊው እየተነገረ ይገኛል
ይህ በዚህ  እንዳለ በአንቀጽ 39 የተቀመጠው ህገመንግስት እስካልተነሳ ድረስ ኢትዮጵያ የመበታተን እድል ሊገጥማት ይችላል ብለው የሚፈሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እጅግ ብዙ ነው : ይህ ፍራቻ የመነጨው ያለምክንያት አይደለም ባለፉት ሁለት አስርት አመታት እንደታየው በርካታ የጎሳና የሃይማኖት ግጭቶች እንዲፈጠሩ በብዙ መሞከራቸውንና ጥቂቶቹም ውጤት ማስገኘታቸውን አይተናል ሆኖም ግን ህዝቡ በራሱ መንገድ ግጭቶቹንና ችግሮቹን በመፍታት እስከ አሁን ድረስ በሰላም ለመኖር ችⶀአል ነገር ግን ከአሁን በሁዋላ ያን አይነት እድልስ ባይኖርስ ብለው የሚሰጉ ብዙዎች ናቸው
ከዚህም በተጨማሪ ውስጥ ለውስጥ ህዝቡን ለእምነቱ እንዲነሳና በበላይነት ሌላውን እንዲገዛ ካልሆነም ኢትዮጵያ እንድትበታተን ነው የምንሰራው በማለት በግልጽ እና በይፋ የነገሩንን እኛን መሳይ ጠላቶቻችንን እንዴት መለየት እንችላለን የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም : በመሆኑም እነዚህ በውጪ ሃይሎች እየተረዱ በፖለቲካ ሽፋን የሃይማኖት ነውጥ ለማስነሳት የሚሰሩ ስመ ኢትዮጵያውያንን ከምንም ጊዜ በበለጠ አንድ ሆነን በመነሳት ላፍታም ሳንዘናጋ መዋጋት የየአንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን የውዴታ ግዴታችን ነው በማለት ብዙዎች ይስማማሉ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአሁኑ ሰአት በሃገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ያለው የእምቢታ እንቅስቃሴ መግታትም ሆነ ማቆም ካልተቻለ ሀገሪቱን በፖለቲካ ሽፋን ለሚንቀሳቀሱ የሃይማኖት ጽንፈኞች አሳልፎ በመስጥትና ከሀገር በመውጣት ያለስጋት መኖር የሚያስችላቸው  ህዝቡ እርስ በርሱ ሲራኮት ከመሆኑም በላይ  እነሱን ተከታትሎ ለፍርድ የሚያበቃ ሌላ መንግስትም ሆነ ሃገር እንዳትኖር ታስቦ የቁርጥ ቀን ማምለጫ እንዲሆኑ የተዘጋጁስ ቢሆንስ በማለት ጥርጣሬአቸውን የሚያሰሙ በቁጥር ጥቂቶች አይደሉም
እናም ታላቁ ባለ ራእዩ መሪ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አለም በቴክኖሎጂ እንደ አንድ መንደር በተቀራረበችበትና በሰለጠነችበት በ21ኛው ክፍለ  ዘመን እኛን እጅግ ፈታኝ እና ዘግናኝ በሆነ የጎሳ ፖለቲካ አደራጅተውን ስላለፉ ከሳቸው በፊት ከነበሩት መሪዎች በላይ የሚወዷትን እና የሚሳሱላትን የሃገራችን ኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለማስከበር የወጠኑት ራእይ እና የነደፉት እቅድ እጅግ በጣም በጣም ሊያስደንቃቸው እና በጣም ሊያስመሰግናቸው ይገባል በማለት ብዙዎች በስላቅ ሹፈት ለሳቸው ያላቸውን ክብር እና አድናቆት ሳይቸሩ አያለፉም ::
ለመረጃ ያህል
የአቶ መለስ ዜናዊ ወርሃዊ ደሞዝ  $2640  ሲሆን ፣ በግላቸው የባንክ አካውንት ያስቀመቱት ገንዘብ መጠን ደግሞ  $ 3 000 000 000 ነው ፣ በአንድ ወቅት ባለቤታቸው ወይዘሮ አዜብ እንዲህ ብለው ነበር በአሁኑ ሰአት በአለም የመጨረሻዎቹ ደሃ የሃገር መሪ ቤተሰቦች እኛ ብቻ ነን የመለስ ደሞዝ ብር 3000 ብቻ ነው በማለት እንደ አሻንጉሊት ለሚቆጥሩት ምክር ቤት ተናግረው ነበር ይሁን እንጂ እውነታው ግን ሌላ ነው በደሞዝ ደረጃ እንኩዋን ቢታይ የአቶ መለስ ወርሃዊ ደሞዝ $2640 እንደሆነ የተዘገበ ሲሆን ይህ ወደ ኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር እንኩዋን በትንሹ አስልተነው
ብር 52800 ይሆናል : ታድያ ወይዘሮ አዜብ እንዴት ቢያሰሉት ነው ብር 3000 የሆነው ሌላወስ $ 3 000 000 000 ወይም
በብር  60 000 000 000 እንዴት ተገኘ ?

meles-with-azeb

 

azeb-mesfin-1የአቶ መለስ ባለቤት የሆኑት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ወርሃዊ ደሞዛቸው ለግዜው ይፋ ባይወጣም ከአቶ መለስ ያነሰ ደሞዝ እንደሚያገኙ ግን የታወቀ ሲሆን ፣ ወይዘሮይቱ በግላቸው አካውንት ያስቀመጡት ገንዘብ መጠን
$2 500 000 000
ወይም በትንሹ አስልተነው
በብር 50 000 000 000  ይሆናል 

azeb-photo

 

 

 

 

 

 

semehal-meles

 

 

 

 

እንዲሁም ከሁለቱ የምትወለደው ሰመሃል መለስ ደግሞ በግል አካውንቱዋ የተቀመተላት የገንዘብ መጥን $5 000 000 000 በትንሹ በብር ብናሰላው ብር  100 000 000 000  እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁለቱ የመለስ ልጆች እና ከአቶ መለስ ውጪ እንደተወለደ የሚነገርለትና ነዋሪነቱን በደቡብ አፍሪካ ያደረገው የወይዘሮ አዜብ ልጅ ደግሞ ስንት ይሆን ድርሻው ወደሁዋላ ተመልሰን የምናየው ጉዳይ ሲሆን አቶ መለስ እና አዜብ ግን ይህን ሁሉ ገንዘብ እንዴት ሊያገኙ ቻሉ በማለት ለሚጠይቁ መልሱ ግልጽ እና አጭር ነው ይህም ከሚራበው እና በችግር ከሚሰቃየው ደሃው ኢትዮጵያዊ አፍ በመንጥቅ ነው ፣ ነገር ግን ይህን እውነታ መቀበል ለማይወዱና ለሚበሳጩ ወዳጆቻቸው እና ጀሌዎቻቸው እንዲህ ብንላቸውስ ምን አልባት ማንም ሳይሰማና ሳያውቅ እንደ ሙሴ ዘመን የዶላር መና ከሰማያ ዘንቦላቸው ቢሆንስ ብለን ትንሽ እየቀለድንባቸው እንዲረጋጉና እንዲያስተውሉ ብናደርጋቸው ሳይሻል አይቀርም
semehal-meles-zenawi

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ለነዚህስ ወገኖቻችን ማን ያስብላቸው ይሆን ?

godana-7 godana-1godana-2godana-3 godana5godana-6

 

 

About the Author

Conclusion- Let Us Walk You Through The Ethiopian History Before And Now With The current Politics !